ይህ ፕሮግራም የሚያተኩረው በራስ ላይ መተማመንና እራስን በመቻል ላይ ይሆናል። ፕሮግራሙን በሥራ ላይ  ለማዋል የተለያዩ ተግባሮችን መዘርጋትና ለችግሩ መፍትሄ የሚሆኑትን ጉዳዮች መቀየስ እነዚህ ተግባሮች ፡-

 

ሀ.       የሲቪል አገልግሎት ክፍል

ስ.       የሕብረተሰብ ዕድገት ክፍል

ሐ.       የሕብረተሰብ ደህንነት ጥበቃ

 

ሀ.      የሲቪል አገልግሎት ክፍል

 

ይህ ክፍል የተሟላ ችሎታ ያላቸዉንና ፈቃደኛ  የሆኑ ምሑራንን ያቀፈ ይሆናል። አገልግሎቱ የሚያተኩረዉ  ሶስት ግቦችን ለኢትዮጵያ አሜሪካዊያን  ወጣቶች ለማቅረብ ይሆናል።

 

ሀ.      ዕዉቀት

ለ.      የሥራ ችሎታ

ሐ.      አመለካከት

 

ሀ.      ዕዉቀት ፡- የኢዮጵያና/አሜሪካን ሕብረተሰብ የሚከተሉትን ተግባራት በሥራ ላይ  ያዉላል።

1.       ሕብረተሰቡን መተርጎምና የት እንደሚኖሩ ይመረምራል።

2.       የአካባቢውን ጉዳዮች ይመረምራል ይተረጉማል።

3.       የተሟላ ሕብረተሰብ ክፍል ለመሆን የሚያበቁትን ሁኔታዎች ያጠናል።

4.        ሕብረተሰቡን የሚመለከቱ ድርጅቶችንና ሕብረተሰቡን የሚያግዱ ፖሊሲዎች                       አጥንቶ ያስረዳል።

5.       ግለሰቦች የሕብረተሰቡን ችግሮች እንዴት እንደሚፈቱ  ያጠናል።

 

ለ.       የሥራ ችሎታ – የኢትዮጵያ/አሜሪካን ሕብረተሰብ የሚከተሉትን ተግባራት በሥራ

       ላይ ለማዋል ይሞክራል።

 

1.       ከሕዝብ መገልገያ መዝገብ ጥናቶችን ይገበያል።

2.      የተገኙትን ጥናቶች ዓላማዎችን ትክክለኛነታቸውንና ትኩረታቸው ይመዘናል።

3.       የተገኙትን ጥናቶች ችግሮችን ለመፍታት ይጠቀምባቸዋል።

4.     ተግባሮችንና ሃላፊነቶችን ከሌሎች ጋር በመተባበር ይፈጽማል።

5.      ከግብ ለመድረስ የሚያስችሉ ልዩ ችሎታዎችን በመጠቀም ታማኝ ውሣኔ   ላይ  ይደርሳል።

6.       ግንኙነትና አሳማኝ የሆኑ ሁኔታዎችን ይገነባል።

 

 

ሐ.       አመለካከት – በኢትዮጵያ/አሜሪካን ሕብረተሰብ የሚገኙ ሕጻናት

 

1.       የተለያዩ ሕብረተሰብን ያውቃሉ ያከብራሉ

2.

3.     የአገልግሎትን ጠቃሚነት ያስረዳሉ በሕብረተሰብ አገልግሎት ላይ  ይሳተፋል።

 

ለ.      የሕብረተሰብ ዕድገት ክፍል

 

ይኽ ቡድን በመታሰቢያ ድርጅቱ ውስጥ ሶስት ዋና ዋና ሚናዎች ላይ ይሳታፋል።

 

1.       ወላጆች በልጆቻቸዉ ትምህርት ላይ እንዲሳተፉ ያበረታታል ይተባበራል።

2.            ሕፃናት የወደፊት መሪዎች ለመሆን የሚያስችላችዉን ስጦታ ይገነባል ይገፋፋል ያበረታታል።

የወደፊቱ የሕብረተሰብ መሪ ለመሆን የሚያበቁ ትምህርት ይሰጣል።

3.           ወጣቶች በሕብረት በቡድን ለአካባቢያቸዉ ተፈላጊ የሆነ ተግባር ፕሮግራም አውጥተው ተግባር

 

1.       ገንዘብ አያያዝ

2.       የስራ ችሎታ

3.     ጤንነት

4.          ለአሰቸኳይ ነገሮች መዘጋጀት

 

 

1.       የገንዘብ አያያዝ – የሚከተሉትን ያጎለብታል

 

ሀ/       የቤተሰብ በጀት  ማውጣት

ለ/       ለጡረታ ዝግጅት ማድረግ

ሐ/       ጥሪት ማዳበር፤ የቤት ባለቤት መሆንና ለኮሌጅ የሚከፈል ገንዘብ ማዘጋጀት

 

2.       የሥራ ችሎታ – ለሚከተሉት ጉዳዮች ያገለግላል ፡-

 

ሀ/       ለሥራ መቀጠር የሚያበቃ ችሎታ ማዳበር፤ የቃል ጥያቄ አመላለስ ማስተማር። የችሎታ ዝርዝሮችን

የሚገልፅ ሰነድ ማዘጋጀት

ለ/       ሥራን የማክበርና ማከናውን የሚያስችል ትምሕርት  መስጠት

ሐ/     በትምሕርት የሚገኘውን ዕድል አጠቃቀም ማሳወቅና ቤተሰብን ለመርዳት  የሚያስችል ሁኔታዎችን

መፍጠር

 

3.       ጤንነት የሚከተሉትን ለማድረግ ይረዳል።

 

ሀ/       የጤና ጥበቃ ለቤተሰብና ለሕብረተስብ ማቅረብ

ለ/       የጥሩ አመጋገብን ጥበብ ማወቅና ለጤንነት  የሚጠቅሙ ምግቦችን መጠቀም

ሐ/       እንቅስቃሴ በማድረግ  ጤንነትን ማዳበር

 

4.       ለአስችኳይና ድንገተኛ ወቅቶች ዝግጅቶች

 

ሀ/       ለድንገተኛ ወቅት የሚሆን ጥሬ ገንዘብ ማስቀመጥ

ለ/       ለቤተሰብ ላንድ ሳምንት የሚሆን የማይበላሽ ምግብ መከዘን

ሐ/       ለድንገተኛ ወቅት የሚሆኑ ቁሳቁሶች ማስቀመጥ

መ/       ቤተሰብ ዘመድና ውዳጅ መገናኛ መስመሮች ማውጣት

 

5.       ቤተሰብን ለመወላጃ ብቃት ማሰልጠን – በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ለመወላጃ የሚጠቅሙ ትምህርቶችን

ዝግጅቱ ይሰጣል።

 

ሀ/       ቤት ውስጥ መጠነኛ ጥገናዎችን

ለ/       መኪና አያያዝና አጠባበቅ

ሐ/       መኖሪያ ቤትንም ሆነ አፓርትመንት ጤናማ በሆን መንገድ አጠባበቅ

 

ሠ.       ሕብረተሰብን ደህንነት ጠባቂ አካል

 

ይህ አካል በሕብረተሰብ ውስጥ ያሉትን ወጣት  ልጆች ደህንነት በውይይት  በመተባበር በማስተማር ተቀዳሚ ተግባሩ ያደርጋል። እንደዚሁም ይህ ቡድን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አዛውንት አባትና እናቶች አካለ ስንኩል/አቅም ላነሳቸው  ግለሰቦችና ቤተሰቦች መከታ የመሆንአገልግሎት  ያበረክታል። ይህንንም በሚከተሉት ዝርዝር ነጥቦች ትኩረት ይስጣል።

 

1.      ቤተሰቦችና በሕብረተሰቡ ውስጥ ያሉትን ጨቅላ ልጆች አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ

ሁኔታዎችን በቀደምትነት ይመረምራል  ያጠናል ያስተጋባል

 

2.     ሕጻናትን ከክፉ አደጋ ለመከላከል ማሕበራዊና ቤተሰባዊ ትብብርን በበጎ ፈቃደኝነት ለመሳተፍ የሚያበቃ ዝግጅታዊ እርምጃ መውሰድ/መከተል

 

3.    ሕፃናትን ከክፉ አደጋ ለመከላከል ትምህርታዊና ንቃተ ሕሊና ማቅረብ በሕብረተሰቡ ዘንድ መገንባት

 

4.      ባለስልጣኖች ሕፃናትን ከአደጋ ለመከላከል ትብብር ለሚደረግላቸው ጥረት የተሟላ ተግባራትን እንዲፈጽሙ መመካከር መዘከር

 

5.      የካሊፎርንያ ሕግ ሕፃናትን ከአደጋ ለመከላከል ያወጣውን ሕጎች ጠንቅቆ ማወቅና ማሳወቅ

 

6.     ሕብረተሰቡ ለሕፃናቶች ከአደጋ ለማዳን የሚደረገውን ጥበቃና ድጋፍ እንዲታወቅ ማድረግ