የትምህርት ፕሮግራሞችን ተቀዳሚ ግብ ማስተማር የሕብረተሰቡን  ተሳታፊዎች የትምህርት ትኩረትና የበለጠ ዕውቀት  እንዲያገኝ ማድረግ ነው። በዚህ ዓላማ የሚሳተፉ ቡድኖች የሚከተሉትን የትምህርት ገበታዎች ለማስተላለፍ ብቃት ያላቸው ይሆናሉ።

1)       በትምህርት ቤትና በከፍተኛ ደረጃ የሚሰጡ ትምህርቶች

2)     በትምህርት ቤት የሚሰጡትን ትምህርቶች አስመልክቶ የማሰልጠኛ ፕሮግራሞች

(ቱተሪንግ)

3)       ትምህርታቸውን ላለመቀጠል  የሚያሰጉ ወጣቶችን መከታተል መደገፍ

4)       በትምህርት ለመግፋት ለሚጣጣሩ አዋቂዎች

5)       ሕብረሰባዊዎችን ለመደገፍ የሚያገለግሉ ትምህርት ቤቶች

6)       በአጠቃላይ የአዋቂዎች ትምህርት

7)       ከሥራ ጋር የተያያዙ ፕሮራሞች

8)       ማንበብና መጻፍ ትምህርት ድጋፍ ሰጪዎች

9)       የሕፃናት ጥበቃና መዋያ ሥፍራዎች

10)       ከትምህርት ሰዓት በኋላ መወላጃ ፕሮግራሞች

 

እላይ የተጠቀሱትን ፕሮግራሞች እሥራ ላይ ለማዋል የይስሃቅ ድረስ የኢትያጵያዊ ድጋፍ ድርጅት እነኚህን ወጣቶች እሚቻላቸውን ግብ እንዲደርሱ ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል። ፕሮግራሙ የተቀየሰው መሪ ግለሰቦች ወጣቶችን አግባባዊ የጤና፤ የሕሊና ሕብረሰብአዊና የአእምሮ ዕድገት እንዲኖራቸው ለመምራት ትምህርት፤ ዕውቀትና ጥበብ እንዲኖራችው በቀደምትነት በማሰናዳት ነው።

 

ድጋፍ ሰጪ ፈቃደኛ ቡድኖች የሚከተሉትን መሠረተ ዓላማዎች በቅንነትና በትጋት እሥራ ላይ ያውላሉ፡-

 

1)       በትምህርት ቤትና በኑሮ ትግል/ችግር ያለባቸውን በማሰተማር

2)      በትምህርት፤ ሕብረሰብአዊ ውስጥ መዋሃድና የመኖር የመማር ሕሊና መፍጠር

3)      ወጣቱ መሠረተ ዓላማና ግብ ሕብረሰቡ ውስጥ ተፈላጊ ለውጦች እንዲመጡ ማድረግ

4)      ከትምህርት በኋላ/በረፍት ጊዜአቸው ጎልማሳ ወጣቶች በግንባታ የሚያሳልፉባቸውን

ፕሮግራሞች ማሰናዳት

የይስሃቅ ድረስ  ኢትዮጵያዊ ድጋፍ ድርጅት ወጣት ኢትዮጵያዊያኖች  ከትምህርት በኋላ ትምህርት ቤት በሚዘጋበትና በቅዳሜና  እሁድ እረፍት ቆይታቸው የተሟላና አርኪ የሆነ ፕሮግራም ኖሮእቸው በሚቀጥሉት ሶስት ዓላማዎች ራሳቸውን የማሻሻል እድል እንዲያገኙ/እንደሚገባቸውም ፍፁም እምነቱ ነው።

 

1)       በትምህርት ቤት ጥሩ ውጤት ማግኘት

2)       በራስ የመተማመንና በጎ አስተሳሰብ

3)       የታረመና ግብረ ገብ ጠባይ ማሳየት

 

ድርጅቱ በተጨማሪ ከትምህርት በኋላ/በረፍት ጊዜ መሰጠት አለባቸው የሚላቸውን ፕሮግራሞች  መኖር አለበት የሚለው በነኚህ አራት ነጥቦች ላይ የተመሰረተ ነው።

 

ሀ/     ፕሮግራሙ ለመማር/ለማጥናት ተጨማሪ እድል በመስጠት ወጣቶቹ በትምህርት ለመላቅ ሕብረሰብአዊ                      ባሕላዊና ለአካባቢው ተሳትፎና ተፈላጊ ጥብብና ንቃት ያስገኛል በማለት

ለ/     የድርጅቱ ፕሮግራም የተሟላና ሕሊናዊ ተፅዕኖ ያለው መስመር በመያዝ የተለያዩ አገልግሎት ማለት

የወላጆች ስብስብና ጥናት፤ የእንግሊዘኛ ትምህርት ወዘተ. ይሰጣል።

ሐ/        ድርጅቱ ከትምህርት በኋላ/በረፍት ጊዜዎች ለወጣቶች ሰላማዊና ግንባታ ያላቸው ፕሮግራሞች

ያለበት አካባቢ በመፍጠር፤ የወጣቶቹ ወላጆች እሥራ ላይ በሚውሉበት ወቅት አጉልና የጥፋት ሥፍራዎች ዘንድ ከመሠማራት እንዲጠበቁ ያደርጋል።

መ/    ከትምህርት  በኋላና/በረፍት ጊዜ የሚሰጠው ፕሮግራም ትምህርት ቤት የሚሰጠውን የበለጠ እንዲገነባና

በተጨማሪ ኮሌጅ ለመግባትና ሥራ ለመያዝ የሚያስፈልጉትን ምክር ይዘክራል።