የጤንነት ፕሮግራም ተፈላጊውን ሕክምና ማሳወቅና ተቀዳሚና አንኳር ዓላማው ሲሆን፤    የሚቀጥሉትን አሳቦችን ይጨምራል።

 

1.    በሽተኛው እንዲመረምረው የሚፈልገውን ሐኪም እንዲያየው የሚያበቃው (ሪፈረንስ) ማስገኘት

2.      ወደ ሕክምና ቦታ ሊደረስ የማይችሉ (ድኩማን) እና አቅም ላነሳቸው የመመላለሻ (ትራንስፖርት) መስጠት

3.       እንግሊዘኛ ለማይናግሩ የማስተርጎምና ቀጠሮ የመውሰድ ተግባራት መስጠት

4.       ለእርጉዞች ተፈላጊውን ምርመራና ምክር መስጠት

5.       በሱስ ለተጠመዱ ተፈላጊውን ዕርዳታ እንዲያገኙ መደገፍ

6.       የቤተሰብ የጤና አያያዝ ትምህርትና ምክር ወደሚገኝበት መምራት

 

በአጠቃላይ የጤንነት ፕሮግራማችን ተቀዳሚ ሥራው ፡-

 

1.       የሕብረተሰቡን የጤንነት ፕሮብሌሞች በቅርብ መከታተል

2.       በሕብረተሰቡ የጤንነትና አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ሁኔታዎች ተንትኖ ማወቅ

3.       የሕብረተሰቡ የጤንነት ሁኔታዎች ማሳወቅ  ማስተማር ራስን ማስቻል

4.      ከሕብረተሰቡ ጋር ያሉትን ጤንነት ጉዳዮች ለመጠቆምና ለማወቅ ጥምር ቅስቀሳ

ማካሄድ

5.      የሕብረተሰቡና የግለሰቦችን ጤንነት ለማሻሻል የሚደረገውን ጥረት መርሆና ፕሮግራ ሞች  ማውጣት

6.      ጤንነት ለመጠበቅ ያሉትን ሕግና ድንጋጌዎችን ማሳውቅ ያም በሌለበት ቦታ

አማራጭ ሁኔታዎችን ማሳወቅ